መልዕክተ ቹ
00:00
00:00
Embed Code (recommended way)
Embed Code (Iframe alternative)
Please login or signup to use this feature.

በመላው አለም የተበታተኑ ግን በአላማ አንድ የሆኑ ኢትዮጵያያውያን በያሉበት ሁሉ ይተጋሉ። ከኒህ ኢትዮጵያውያን መካከልም የ ኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች መወያያ መድረክ ታዳሚዎች በየሀገራቱ ጉልህ ሚና እየተጫወቱ ነው። ያንን በተመለከተ ትንሽ ብለናል። የቅራኔ አፈታታችን ማሸነፍ ወይም መሸነፍ እየበዛበት በቀላሉ ሊፈቱ የሚችሉ ጉዳዮች እየከረሩ አጥፊና ጠፊ እያረጉን ነው። ይህ በፖለቲካም በማህበራዊም ሆነ ሀይማኖታዊ ተቋማት ሁሉ እየተንጸባረቀ ነው። በዚህ ጉዳይም ለውይይት መንደርደርያ ያህል ምሳሌዎች ቀርበዋል። የትግራይ ተገንጣይ ድርጅት መሪዎች አባሎችና ደጋፊዎቻቸው በስህተት ላይ ስህተት በጥፋት ላይ ጥፋት እያከሉበት በመጨረሻ የግራዚያኒ ትቆርቋሪ ሆነው ኢትዮጵያውያንን በጅምላ ማሰራቸው እጅግ አሳሳቢና አነጋጋሪ ጉዳይ እንደሆነ ተዘክሮአል ስነ ግጥም ቀርቦአል። የመሰብሰብ ነፃነትን የመወያየት ነፃነት የተሟጠጠበት ሀገር መሆኑንም በሰማያዊ ፓርቲ ላይ የደረሰውን በደል እንደምሳሌ አቅርበናል።
ለማፈን በሞከሩ ቁጥር ጫካ እያሉ ሲጥፉት እንደነበረው ቁምጣ አፈናውን ከአንዱ ሲሰፉት ከሌላው ሲቀደድ አሁን ክፋታቸው ሁሉ እርቃኑን እየወጣባቸው ሄደዋል። ይህ እርቃኑን የወጣ ጭፍጨፋና ሀገር ማፍረስ ደግሞ ኢትዮጵያውያንን የበለጠ አንድ እያደረገ የሚመጣ በመሆኑ ተስፋ የሚሰጥ እንጂ ተስፋ የሚያስቆርጥ ያለመሆኑን በመግለጽ የሚያበቃ ፕሮግራም ነው።

Licence : All Rights Reserved


X